Dialog Box

What is palliative care? - Amharic

What is palliative care? - Amharic

የማስታገሻ እንክብካቤ ምንድን ነው?


የማስታገሻ/Palliative እንክብካቤ የማያገግም በሽታ ላለባቸው ሰዎች የሚሰጥ የጤና እንክብካቤ ነው። ለታካሚዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ምቾት ድጋፍ እና የህይወት ጥራት ላይ ያተኩራል። ሰዎች የቻሉትን ያህል ለቻሉት ጊዜ እንዲኖሩ ይረዳቸዋል።

  

የማስታገሻ እንብካቤ መቼ ሊጀምር ይችላል?  

የማስታገሻ እንክብካቤ በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ወይም ቀናት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ህመም ሲኖር ሊጀምር ይችላል። በብዙ አጋጣሚዎች አንድ ሰው ለሕመሙ ሌሎች ሕክምናዎችን በሚወስድበት ጊዜ የማስታገሻ እንክብካቤ ሊያገኝ ይችላል።

የማስታገሻ እንክብካቤ የሚሰጠው ማነው? 

የማስታገሻ እንክብካቤ በማንኛውም የጤና ባለሙያ እንደ አጠቃላይ ሐኪም፣ የህክምና ባለሙያ ወይም ነርስ ሊሰጥ ይችላል።

የአንድ ሰው ምልክቶች ይበልጥ ውስብስብ በሚሆኑበት ጊዜ ልዩ ወይም ስፔሻሊስት የማስታገሻ የእንክብካቤ አገልግሎቶች ሊሰጡ ይችላሉ።  ብዙውን ጊዜ የሚመሩት እንደ ጠንካራ ህመም፣ ማስታወክ እና የመተንፈስ ችግር ያሉ የህይወት መጨረሻ ምልክቶችን በመቆጣጠር ላይ በተካነ ዶክተር ወይም ነርስ ነው።

የስፔሻሊስት የማስታገሻ እንክብካቤ ቡድን ከአንድ ሰው ነባር የጤና እንክብካቤ ቡድን ጋር በመተባበር መስራቱን ይቀጥላል እና የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል:-

  • ዶክተሮች 
  • ነርሶች 
  • የተባበሩ የጤና ባለሙያዎች 
  • ፋርማሲስቶች 
  • የሥነ ልቦና ባለሙያዎች 
  • መንፈሳዊ ወይም የመንፈሳዊ እንክብካቤ ሰራተኞች 
  • የማስታገሻ እንክብካቤ በጎ ፈቃደኞች

ልዩ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

ወደ ልዩ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶች ሪፈራል በግለሰብ ወይም በቤተሰብ አባል ወይም ተንከባካቢ ወይም በማንኛውም የጤና ባለሙያ ሊደረግ ይችላል።

ልዩ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶች ምን ዓይነት እንክብካቤ ይሰጣሉ?

ልዩ ማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-  

  • ውስብስብ አካላዊ የህመም ምልክቶችን ለመቆጣጠር ይረዳል
  • በማህበራዊ፣ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች ጋር የተገናኘ ድጋፍ ይሰጣል 
  • ለበሽተኛው እና ለቤተሰቦቻቸው ወይም ለተንከባካቢዎቻቸው የምክር እና የሀዘን ድጋፍ ይሰጣል

ልዩ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶች የት ሊሰጡ ይችላሉ?  

የማስታገሻ እንክብካቤ በነዚህ ስፍራዎች ሊሰጥ ይችላል:-    

  • ቤት ውስጥ 
  • ሆስፒታል ውስጥ 
  • በማገገምያ ውስጥ 
  • በአረጋውያን የእንክብካቤ መኖሪያ ቤት ውስጥ
  • በሚደገፍ የአካል ጉዳተኞች ማረፊያ ውስጥ

ልዩ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶች ምን ያህል ያስከፍላሉ? 

አብዛኛዎቹ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶች ነፃ ናቸው። አስፈላጊ ከሆነ ከእርስዎ ጋር የምንወያይባቸው የመድኃኒቶች ወይም የመሳሪያዎች አንዳንድ ወጪዎች ሊኖሩ ይችላሉ።  

ለቤተሰብ እና ለተንከባካቢዎች ምን ዓይነት ድጋፍ አለ?  

ልዩ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎቶች ለቤተሰቦች እና ተንከባካቢዎች ተግባራዊ እና ስሜታዊ ድጋፍ ይሰጣሉ።

አስተርጓሚ ቢያስፈልግስ?

ሲመጡ አስተርጓሚ እንደሚያስፈልግ ለአገልግሎቱ ማሳወቅ አስፈላጊ ነው።

እንዴት አገልግሎት ማግኘት እችላለሁ ወይም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እችላለሁ? 

  • ሐኪምዎን፥ ልዩ ባለሙያተኛዎን ወይም ማንኛውንም የጤና ባለሙያ ያነጋግሩ
  • ወደ የአካባቢዎ የማስታገሻ እንክብካቤ አገልግሎት ይደውሉ
  • የቪክቶሪያ የማስታገሻ እንክብካቤን (Palliative Care Victoria) ያነጋግሩ 
    • ስልክ ቁጥር 03 9962 9644 (ከጠዋቱ 9 ሰዓት እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት፣ ከሰኞ እስከ አርብ) 
    • ኢሜይል፦ info@pallcarevic.asn.au

የስልክ አስተርጓሚ ማዘጋጀት ይቻላል። እባክዎን የትኛውን ቋንቋ እንደሚፈልጉ ይንገሩን?




Further Resources

What is palliative care? - Amharic DOWNLOAD FLYER
How palliative care can help - Amharic DOWNLOAD FLYER


Donate